+251-116-463-357
486
Monday to Friday - 8:30 Am to 5:30 Pm
Do you have any questions ?
Home
ABOUT US
Service
Cement
Artisanal
Fertilizer
Marble
Metallic
Research_Document
Headships
Event
E-Library
×
Digital Research doc Coming Soon
የማዳበሪያና የሌሎች ኬሚካል ግብዓት ልማት ምርምር ዴስክ
መግቢያ
የማዳበሪያና የሌሎች ኬሚካል ግብዓት ልማት ምርምር ዴስክ በ2016 በጀት ዓመት ለሚያከናውናቸው ተግባራት በቅድሚያ ዓመታዊ መሪ ዕቅድ በማዘጋጀትና ቀጥሎም የበጀት ዓመቱን በሩብ በመከፋፈል በየጊዜው የሚመራበትን ዕቅድ በማውጣት ወደ ተግባር ለመግባት በእንቅስቃሴ መሆናችንን ይታወቃል፡፡ ምርምር ዴስኩ ኢንስቲትዩቱ ለበጀት ዓመቱ ያቀዳቸውን ዕቅዶች መሠረት በማድረግም ለሚታቀዱ ዕቅዶች የሚከናወኑ ተግባራትን በስፋትና ጥልቀት እየገመገመ እንዲሁም በየጊዜው የሚወርዱ አዳዲስ ተልዕኮዎችን በማካተት ዕቅዱን እንደገና የመከለስና ከኢንስቲትዩቱ ተልዕኮና ፍላጎት ጋር የማጣጣም ሥራ ይሠራል፡፡ በመሆኑም የማዕድን ልማት ስትራቴጂውን የትኩረት አቅጣጫ መሰረት በማድረግ ንዑስ ዘርፉ የ2015 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀሙን በጥንካሬና በድክመት ለይቶ ገምግሟል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘም በ2015 በጀት ዓመት በአፈፃፀም የታዩ ጠንካራ ጐኖች በ2016 በጀት ዓመት ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ድክመቶች ደግሞ እንዳይደገሙና እንዲስተካከሉ አቅጣጫ በማስቀመጥ የሚቀጥሉ አስፈላጊ ዕቅደችን በማዘጋጀት ወደ ፈጻሚው የማውረድ ስራ በመሰራት ላይ ነው፡፡ ስለሆነም የንዑስ ዘርፉ የ2016 በጀት አመት ስራዎችን አፈፃፀም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የማዳበሪያና የሌሎች ኬሚካሎች ጥናትና ምርምር በተመለከተ የተከናወኑ ተግባራት
በግብርና ሚኒስቴር እና በማዕድን ሚኒስቴር በትብብር በተቀረጸው የአፈር አሲዳማነትን በግብርና ኖራ የማከምና የግብርና ምርታማነትን የማሻሻልና የማሳደግ አገራዊ ፕሮጀክት መነሻ በማድረግ የ2016 በጀት ዓመት የግብርና ኖራ አቅርቦት እና ስርጭት ማስፈጸሚያ ዕቅድ መርኀ-ግብር በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ፣ በአማራ፣ በሲዳማ ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች በ2016 በጀት ዓመት ለማከም የታቀደውን 100 ሺ ሄክታር እውን ለማድረግ መሰራት ያለባቸውን የአድሚኒስትሬሽንና የኦፕሬሽን ስራዎች እና የሚያስፈልገው አጠቃላይ ወጪ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡