• icon+251-116-463-357
  • icon486

Monday to Friday - 8:30 Am to 5:30 Pm

Marble , Granite & Glass Minerals Development & Research

የማርብል ግራናይትና መስታወት ልማትና ምርምር ዴስክ

የኢትዮጵያ ጂኦሎጂ እጅግ በጣም ብዙ የተለያዩ ማዕድን ሃብት ያቀፈ ነው ። በሀገሪቱ ኢግኒየስ (igneous) አለቶች 23 % እና ሜታሞርፊክ ( metamorphic) አለቶች 25% የሚሸፍን ሲሆን እያንዳንዳቸው እንደ ማርብል እና ግራናይት ያካትታሉ ፡፡ የማርብል አለቶች የሚፈጠረው ላይም ስቶን በከፍተኛ ግፊትና ሙቀት ውስጥ ሲያልፍ የሚፈጠር የአለት አይነት ነው፡፡ በዋነኛነት ካልሲም ካርቦኔትን የየዘ ሲሆን ሌሎች እንደ ሲልካ ፣ ማግኒዚየም ካርቦኔት ፣ አይረን ኦክሳይድ እና አሊሚኒም ኦክሳይድ አካቶ ይዟል ፡፡ ግራናይት የኢግኒየስ አለት ሲሆን የሚፈጠረውም ከመሬት በታች እሳተ ጎሞራ አካል ማግማን በመፍሰስ ለረዥም ግዜ በመቀዝቀዝ እና በመጠንከር ሂደት ውስጥ የሚፈጠር ነው ፡፡ ግራናይት ውሀን በቀላሉ የማያሳልፍ ፣ የተለያየ የአየር ጠባይን እና የኬሚካል በመቻሉ በጣም ጥሩ የግንባታ ቁሳቁስ ያደርገዋል፡፡ በኢትዮጵያ ከፍተኛ መጠን ያለው የማርብል ክምችት በምዕራብና ሰሜን የሀገራችን ክፍል ይገኛል፡፡ አብዛኛው የእምነበረድ ክምችት ነጭ ቀለም ያለው እምነበረድ የላይም ስቶን መጠኑም እስከ 98 በመቶ ሆኖ የተገኘና በውስጡ ብዙ ኢምፒዩሪቲ የሌለው ነው፡፡ እንደ የሸክላ ማዕድናት፣ የብረት ኦክሳይድ ወይም ቢቱሚነስ የያዘ እብነ በረድ፣ ግራጫ፣ ሐምራዊ፣ ቢጫ፣ ወይም ጥቁር ከለር ሊኖረው ይችላል። የግራናይት አለት ቀለም በውስጡ የያዘው ሚኒሮሎጂ የሚወሰን ሲሆን በተለይም በውስጡ የሚገኘው የፊልድስፓር ጥንቅር የግራናይት ከለር ላይ ተጽዕኖው የጎላ ነው፡፡ፊልድስፓር ቀለል ያለ ቀለም ያለው ቢሆንም የመጠኑ መብዛት ሐምራዊ ግራናይት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ የጂኦሎጂ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የማርብል ክምችት ከለርና መጠን ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ( መተከል ዞን፣ ባፑሪ፣ ሞራ፣ ቡለን፣ እኮንቴ፣ ባሩዳ፣ ማንኩሽ ፣ ዳለቲ) ምዕራብ ትግራይ ፣ትግራይ ምዕራባዊ ዞን (አዴት ፣ ቆላ ተምቤን ፣ መደባይ ዛና ፣ አዲ አሰሪ ) የተለዩ አካባቢዎች ናቸው፡፡ ግራናይት ከሚገኝባቸው በተለይም በሰሜኑ ሀገራችን ክፍል ትግራይ ምስራቅ ዞን ( ከዛላምበሳ) ሰሜን ትግራይ ( እምባምድር ፣ አሰግደ-ጺምባላ ወረዳ) ምዕራብ ትግራይ ( እምባምድር፣ ከራማ ፣ አክሱም ፣ሊላይ አዲያቦ ወረዳ፣ ነጋሽ ወረዳ ) እና በምስራቁ የሀገራችን አካባቢዎች ኦሮሚያ (ባቢሌ) ፣ ሀረር-ድሬዳዋ መንገድ (ሀሳንጌ ፣ ስቁል ) , ምዕራብ ኢትዮጵያ (ጎጃም ፣ ወለጋ-ቡሬ መንገድ ፣ አንገርጉተን ) ,ቤኒሻንጉል (መተከል ዞን፣ሞራ) ይገኛሉ ፡፡

ዓላማ በሀገራችን በኢትዮጵያ የኮንስትራሽህን ኢንዱስትሪ ግብዓት ማድናት ሀብት በምን ያህል መጠን፣ አይነት እና ቀለማት ያላቸው አለቶች በተለያየ አካባቢዎች እንደሚገኙ ባለሀብቱን ኢንቭስ እንዲያደርግ ማስቻል ነው፡፡

የማርብልና ግራናት ጥቅሞች

የማርብልና ግራናት ምርቶች ልስላሴ፣ የማንጸባረቅ ችሎታ እና በጥንካሬ የመቆየት ችሎታ 80 በመቶ ጥቅም ላይ የሚውለው ለኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ግብዓት ለምሳሌ (ለቤት ውስጥ ለወለል እና የግርግዳ ንጣፍ /tiles/ ፣ ለውጫዊ ግርግዳ ህንፃ ግንባታ ፣ ለመስኮት ሲል፣ ለምግብ ጠለፔዛ ንጣታፍ ስራ ፣ ለደረጃ መወጣጫ፣ የወጥ ቤት ጠረፔዛ ንጣፍ እና የእጅ መታጠቢያ ጠረፔዛ ንጣፍ ) ሲሆን ቀሪው ኢንዱስትሪው ግብዓት በመሆን የተለያዩ ምርቶችን እንዲያመርቱ የሚያስችሉ ናቸው ፡፡

About